Radical Tutor
ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በመደበኛ ትምህርት ውስጥ የሚካተቱ 11 የሙያ ዘርፎች ይፋ ሆኑ::
በሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ብቁ የሆኑ አምራች ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችል አዲስ የትምህርት አሰራር ተግባራዊ ሊደረግ ነው።
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በተሻሻለው የቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ መሰረት፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠናዎችን ገና ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ በመደበኛ ሥርዓተ ትምህርቱ ውስጥ የማካተት ስራ ይከናወናል።
ይህንን አዲስ አካሄድ አስመልክቶ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ፣ በሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮች እና በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲኖች መካከል የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ (የአዲስ አበባ መስተዳድር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ)፦ አዲሱ አሰራር ተማሪዎችን በንድፈ ሀሳብ ብቻ ሳይሆን በተግባራዊ ክህሎት በመቅረጽ፣ ውጤታማና አምራች ዜጋ አድርጎ ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ (የሥራና ክህሎት ቢሮ የዘርፍ ኃላፊ)፦ የሥራ ገበያው የሚፈልገውን የበቃ የሰው ኃይል ለማቅረብ የተቀናጀ አሰራር ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።
ለትግበራው አስፈላጊ የሆኑ የመርሃ ትምህርት (Curriculum)፣ የተማሪ ሞጁሎች እና የመምህራን መመሪያዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅተው ተጠናቀዋል።
በመደበኛ ትምህርት ውስጥ የሚካተቱት 11 የሙያ ዘርፎች፦
1. ብረታ ብረት ቴክኖሎጂ
2. አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ
3. አልባሳት ቴክኖሎጂ
4. ህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ
5. ቧንቧ ሥራ
6. ሶፍትዌር ማበልጸግ
7. ሰብል አመራረት
8. ጤና ክብካቤ አገልግሎት
9. ሆቴል አገልግሎት
10. ፀጉር ሥራና ውበት አገልግሎት
11. ምግብ ዝግጅት
ሆነዋል::
Via የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ
24 ·