English
Open in Telegram

Post የሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።

14 September 2026
R
Radical Tutor
የሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ። ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም፣ እና በሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህ ላይ ተመስርቶ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህም መሰረት ከታችን የተገለጸውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለሪሚዲያል መርሃ ግብርየዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል። 1. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 240 እና ከዚያ በላይ (40%) 2. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 228 እና ከዚያ በላይ (38%) በልዩ ድጋፍ የሚታይ የተማሪ ምድብ 1. ከአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%) 2. ከአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%) 3. በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውር ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ500 ውስጥ 185 እና ከዚያ በላይ (37%) 4. በተፈጥሮ ወይም በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ መስማት የተሳናቸው ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%)
39 ·

Nearby in the feed

RRadical Tutorእንኳን ለ2019 ዓመተ ምህረት አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ ! አዲሱ ዓመት የፍቅር፣ የስኬት፣ የማስተዋል እና የአንድነት ዓመት ይሁንልን። መልካም በዓል ! እወዳችኋለሁ ፡፡RRadical TutorPhoto
this message
RRadical Tutorhttps://www.youtube.com/watch?v=nOZBJORl0H4&t=9sRRadical TutorFile
RRadical TutorRadical Tutor@RadicalTutorial · channel · Education
296posts in the index
Venue feed Open in Telegram

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · Index limits · Remove a page · Catalog · Search · How we count