English
Open in Telegram

Post Git እና GitHub ምንድን ናቸው?

20 March 2026
S
Softwares and codes👨‍💻
ReplyPhoto
Git እና GitHub ምንድን ናቸው? በዚህ በሰለጠነ የቴክኖሎጂ ዘመን፤ Developers አንድን ሶፍትዌር ሲሰሩ ብቻቸውን ወይም በቡድን ሆነው ሊሆን ይችላል። ታዲያ የጻፉት ኮድ እንዳይጠፋባቸው፣ የተሳሳቱትን ለማስተካከል ወደ ኋላ ለመመለስ እና በጋራ ለመስራት አንድ ትልቅ መፍትሄ አላቸው 👉 Git & GitHub. Git ማለት Version Control System ነው። ለማስረዳት ያህል፦ አንድን ኮድ ስትጽፉ የዛሬውን ስራችሁን "Save" አድርጋችሁ ነገ ሌላ ነገር ብትጨምሩበትና ብታበላሹት፣ Git ወደ ትላንትናው ስራችሁ በሰላም እንድትመለሱ ይረዳችኋል። ባጭሩ የኮዳችሁ "ታሪክ መዝጋቢ" ነው ማለት ይቻላል። GitHub ደግሞ በ Git የሰራችሁትን ኮድ በኢንተርኔት (Online) የምታስቀምጡበት ቦታ ነው። ልክ ፎቶዎቻችሁን Google Drive ወይም iCloud ላይ እንደምታስቀምጡት ሁሉ፣ GitHub ደግሞ የኮድ ማከማቻ ፕላትፎርም ነው። በዓለም ዙሪያ ካሉ ሰዎች ጋር በጋራ ለመስራትና የሰራችሁትን ስራ ለሌሎች ለማሳየት (Portfolio) በጣም ወሳኝ ነው። Git & GitHub በዋናነት ለምን ይጠቅማሉ? ➤ የኮድ ለውጦችን ለመከታተል (Tracking history) ➤ በቡድን ሆኖ በአንድ ፕሮጀክት ላይ ለመስራት (Team collaboration) ➤ ለነፃ የሶፍትዌር ስራዎች (Open-source projects) ➤ የሰራችሁትን ስራ ለሰው ለማሳየት (Portfolio hosting) በቀላል አገላለጽ፦ Git በኮምፒውተራችሁ ላይ ኮዳችሁን ይቆጣጠራል፣ GitHub ደግሞ ኮዳችሁን ለዓለም ያጋራላችኋል! 🌍 ጽሑፉን ከወደዳችሁት 👍,❤️ አይረሳ። 😊 📌 እስኪ እናንተ ደግሞ GitHub አካውንት ያላችሁ የ GitHub Username-አችሁን comment ላይ ጻፉልን? 👇 ✍️ @softwareAndCodes #Git #GitHub #VersionControl #Programming
9 · 762 ·

Nearby in the feed

SSoftwares and codes👨‍💻Have you ever read some code so horrible you were ready to fight the developer… only to realize the developer was you? 🤣 Yeah… that was me recently. I opened a SSoftwares and codes👨‍💻Photo
this message
SSoftwares and codes👨‍💻This post has changed entire worldSSoftwares and codes👨‍💻Photo
SSoftwares and codes👨‍💻Softwares and codes👨‍💻@softwareAndCode · channel
714subscribers274average post reach
Venue feed Open in Telegram

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · Index limits · Remove a page · Catalog · Search · How we count