Radical Tutor
Photo
ለክረምት ሥልጠና ፈላጊ ተማሪዎች በሙሉ
````````````````````````
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በኤሌክትሮኒክስና በኮምፒውተር ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ በፅንሰ-ሐሳብ እና በተግባር የተደገፈ የክረምት ሥልጠና በነጻ ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቅቆ ሐምሌ 7 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ወራት በአካዳሚው STEM ማዕከል ይካሄዳል።
ስለዚህ የትምህርት ደረጃችሁ ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሆነና ከፍተኛ የትምህርት ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ምዝገባው በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ግቢ ስለሚካሄድ ከወዲሁ ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን።
📍ቦታ:- ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ፤ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ
አለፍ ብሎ በወረዳ 8 ፖሊስ ጽ/ቤት በኩል ገባ ብሎ።
ለጉግል ካርታ (Google Maps)
በፖስተሩ ላይ ያለውን QR ኮድ ይጠቀሙ።
37 ·