English
Open in Telegram

Post የአዳሪ ትምህርት ቤቶች ጉዳይ ፦

30 August 2026
R
Radical Tutor
የአዳሪ ትምህርት ቤቶች ጉዳይ ፦ 1. የትምህርት ስርዓታችን ጉብዝናን መሸለም ልፋትንና ውጤትን ማክበር የጀመረ ይመስላል ። ከሰሞኑ ከ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት ጋር ተያይዞ በአዳሪ ት/ቤቶች ላይ ብዙ አሉታዊ አስተያየቶችን አነበብሁ። አስተያየቶቹ ሲጨመቁ "ጎበዝ ተማሪ ሰብስበው አስገብተው ሁሉንም ተማሪ ፈተና አሳለፍን ብለው ይፎክራሉ "የሚል ነው ። እኔም እላለሁ የአዳሪ ት/ቤቶቹ ዓላማ የ12ኛ ክፍል ፈተናን አስፈትኖ ዩኒቨርስቲ ማስገባት አይደለም !! ት/ቤቶቹ የሻለ አቅም እና ልምድ ያላቸውን መምህራንን ፣ ጎበዝ የትምህርት ስራ አስተዳዳሪዎችን ፤ ጥሩ የቤተመፃህፍትና የቤተሙከራ ክፍሎችን ይዘው የተዋቀሩ ናቸው ። በዋናነት ልጆቹ ከሶሻል ሚዲያ ጫጫታ ተጠብቀው ፤ ቀልባቸውን ሰብስበው የሚማሩበት ነው። ከመደበኛ ትምህርት በተጨማሪ በኮዲንግና ኤአይ አይነት ስልጠናዎችን የሚያገኙበት ነው። እና ይሄ ሁሉ ኢንቨስትመንት መደበኛ ተማሪ ሊያሳካው የሚችለውን የ 50% ማለፊያ ውጤት እንዲያመጡ አይደለም ። ይልቅ ልጆቹ ለዓመታት ላደረጉት ትጋት እና ላመጡት ውጤት ሲስተሙ የሰጣቸው ሽልማትና እውቅና አድርገን ብንረዳው መልካም ነው ። ለ ልዩ ችሎታ እና ተሰጥኦ የሚደረግ ልዩ ጥበቃ እና እንክብካቤ ዓይነት ። 2. ዝቅተኛ የትምህርት ተሰጥኦ ያላቸውን ልጆች ወደ አዳሪ ት/ቤት ሳይሆን የልዩ ፍላጎት ዓይነት ስርዓት ፈጥረን ቴክኒክ እና ሙያ ላይ ብናበረታቸው መልካም ይመስለኛል። 3. የተፈተነ ሁሉ ዩኒቨርስቲ መግባት አለበት የሚል አቋም ልክ አይደለም ። ይልቅ የልጆቹ ውጤት እንደ ሀገር ለ ትምህርት ላለን ጠንጋ*ራ 😀 ዓይን ፤ በልባችን ለሰፈነው ንቀት እንደ መስታወት ነው ። ወላጅ ለልጁ ሀላፊነት ይውሰድ ። ልጅን ት/ቤት በመላክ ብቻ ተዓምር እንዲፈጠር መጠበቅ ሞኝነት ነው ። ቢያንስ ማንበብና መፃፍ መቻሉን ማረጋገጥ ግድ ይላል። ሀገር በቲክቶከር ጫጫታና ሁከት ሳይሆን በጥራት በተማሩ ዜጎቿ ልክ ታድራለች ። ሻሎም !
27 ·

Nearby in the feed

RRadical Tutorየሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ =============================== በአገራችን እየተመዘገበ ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠልና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የአገሪቱን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰለጠነRRadical Tutor#ጥቆማ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በቅድመ-ምረቃ መደበኛ መርሐግብር (በመንግሥት ስኮላርሺፕ እና በግል ክፍያ) እንዲሁም በማታና ተከታታይ መርሐግብር አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። መስፈርቶች ➻ በ2015፣ 2016፣
this message
RRadical Tutorየአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ፕሬዝዴንሻል ስኮላርሺፕ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም 200 (ሁለት መቶ) ልዩ የፕሬዝዴንሻል ስኮላርሺፕ ዕድል አዘጋጅቷል። በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ RRadical Tutorናሳ ወደ ጠፈር ቴሌስኮፕ አመጠቀ የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ጣቢያ (ናሳ) ለጠፈር እና ጋላክሲ ምርምር እና ጥናት አዲስ ቴሌስኮፕ ማምጠቁን አስታወቀ። ቴሌስኮፑ ከፀሐይ ስርአት ውጭ የሚገኙ ፕላኔቶችን፣ በርባኖስ (ብላክ ሆል)፣ ሩቁን የጨለማ ክፍልን ጨምሮ
RRadical TutorRadical Tutor@RadicalTutorial · channel · Education
296posts in the index
Venue feed Open in Telegram

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · Index limits · Remove a page · Catalog · Search · How we count