English
Open in Telegram

Post የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ፕሬዝዴንሻል ስኮላርሺፕ

31 August 2026
R
Radical Tutor
Photo
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ፕሬዝዴንሻል ስኮላርሺፕ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም 200 (ሁለት መቶ) ልዩ የፕሬዝዴንሻል ስኮላርሺፕ ዕድል አዘጋጅቷል። በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ፣ የተቀመጡ መመዘኛዎችን የሚያሟሉ እና ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና በብቃት የሚያልፉ ተማሪዎች የስኮላርሺፕ ዕድሉ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ተብሏል፡፡ የ Presidential Scholarship Program ዕድሉ ተጠቃሚዎች፣ ዩኒቨርሲቲው ባሉት ሰባት ኮሌጆች እና የሕግ ትምህርት ቤት ስር ባሉ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ይመደባሉ። ነጻ የትምህርት ዕድሉ ሙሉ ነፃ የትምህርት ዕድል፣ መጠነኛ የኪስ ገንዘብ እና ከአጋር ተቋማት ጋር በሚኖር ትብብር ተጨማሪ ድጋፍና የስልጠና ዕድሎችን ያስገኛል፡፡ በዚህ የትምህርት ዕድል በወጥነት ተጠቃሚ ለመሆን፣ የዕድሉ ተጠቃሚዎች በየሴሚስተሩ አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.50 እና ከዚያ በላይ ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም የዕድሉ ተጠቃሚዎች በተመደቡበት የትምህርት ዘርፍ መቀጠል ይኖርባቸዋል። የዚህ ስኮላርሺፕ ተጠቃሚዎች በቀጣይነት ዩኒቨርሲቲው የድኅረ-ምረቃ (Masters እና PhD) የትምህርት ዕድል ያገኛሉ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የ2019 ዓ.ም ምዝገባ እስከ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም እንደሚከናወን መገለፁ ይታወቃል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ 👇 https://admission.aau.edu.et/UGAnnouncements @tikvahuniversity
20 ·

Nearby in the feed

RRadical Tutor#ጥቆማ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በቅድመ-ምረቃ መደበኛ መርሐግብር (በመንግሥት ስኮላርሺፕ እና በግል ክፍያ) እንዲሁም በማታና ተከታታይ መርሐግብር አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። መስፈርቶች ➻ በ2015፣ 2016፣ RRadical Tutorየአዳሪ ትምህርት ቤቶች ጉዳይ ፦ 1. የትምህርት ስርዓታችን ጉብዝናን መሸለም ልፋትንና ውጤትን ማክበር የጀመረ ይመስላል ። ከሰሞኑ ከ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት ጋር ተያይዞ በአዳሪ ት/ቤቶች ላይ ብዙ አሉታዊ አስተያየቶችን አነበብሁ። አስተያየቶቹ ሲጨመቁ
this message
RRadical Tutorናሳ ወደ ጠፈር ቴሌስኮፕ አመጠቀ የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ጣቢያ (ናሳ) ለጠፈር እና ጋላክሲ ምርምር እና ጥናት አዲስ ቴሌስኮፕ ማምጠቁን አስታወቀ። ቴሌስኮፑ ከፀሐይ ስርአት ውጭ የሚገኙ ፕላኔቶችን፣ በርባኖስ (ብላክ ሆል)፣ ሩቁን የጨለማ ክፍልን ጨምሮ RRadical Tutorhttps://www.youtube.com/watch?v=PWMmD6f6WcI
RRadical TutorRadical Tutor@RadicalTutorial · channel · Education
296posts in the index
Venue feed Open in Telegram

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · Index limits · Remove a page · Catalog · Search · How we count